Search This Blog

Saturday 14 January 2017

የኮሌጅ ትዝታ
ግልባጭ ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች

((((((((((((((((((((((((((((((((())))))))))))))))))))))))))))
ትዝታ 1, ኮሌጅ እና ፖለቲካ
@@@@@@@@@
"የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች" እንደተባልን የመጀመሪያው ምርጫ ትምህርት ክፍል መረጣ ነው። የእኛ የመጀመሪያ ምርጫ የነበረው ግን "ዱርየ እንሁን ወይስ አንሁን" የሚለው ነው። በአብላጫ ድምፅ ዱርየ እንድንሆን ተወሰነ። ነብር የገደልን ይመስል ፀጉር አሳደግን፣እንደ ጀግና ጆሮ ጉትቻ አደረጉ (እኔ ጆሮ መበሳት ስለማይመቸኝ አልተበሳሁም) ሱሪያችንን ዝቅ አደረግን፤ የግቢውን አቧራ ለመከላከል በሚል ሱሪያችንን ከታች አጥፈን በብር ማሰሪያ ላስቲክ አሠርን። ቆይቶ ላስቲኩ አልበረክት ቢለን በኮንዶም ጫፍ ማሰር ጀመርን። ከተማ ገብተን በ2 ብር 8 ሙዝ 4ቱን በብር 4ቱን አጭበርብረን ገዝተን መብላት ሙዳችን ሆነ። ዱርየዎች ሆንን። ፑል ቤት 1ሰው ቁማር ለመብላት 3 ሰው አሰለፍን። የግቢ በር እየተዘጋብን ከጅብ ጋር እየታገልን በጫካ መግባት ጀመርን። (የእኛ ግቢ ከአንድ በኩል ሙሉ ለሙሉ ጫካ ስለነበር አጥር አልነበረውም። ስለዚህ ፈሪ ካልሆንክ በቀር በር ተዘግቶብህ ውጭ አታድርም) እንዲህ እንዲህ እያልን የመጀመሪያው መንፈቅ አመት ተጠናቀቀ። የዱርየው ቡድን አብዛኛው ሰው በውጤት ሰቃይ ሆኖ ተገኘ።'እነዚህ ልጆች ሰው እያዘናጉ' ተባለ። እኛ ክፍል ደንግጦ ነው መሰለኝ የሰቀለብን Miskir Agegnehu ነው። መጨረሻ ላይ ግን Yayesew Shimelis ጠቀለለን። ቆይቶ እኔ እና ምስክር ከአንደኛው መምህር ጋር ተጣላን። ምስክርን ሽማግሌው በእርግጫ ሲመቱት እኔ ፀጉርህን ሳትቆረጥ እንዳትገባ ተባልኩ። የመምህሩ እግር አነሳስ አሁንም አይኔ ላይ አለ። ከክፍል መቅረት የማይታሰብ ስለነበር እኔ በማግስቱ ፀጉሬን ተቆርጨ ገባሁ። "ቲቸር ይሄው ተቆረጨ መጣሁ" ብላቸው "እኔ እኮ ትንሽ አጠር አድርገው ነበር እንጂ እንዲህ ተቆረጠው አላልኩም" ብለው አስፈቱኝ (አናደዱኝ)። ነፍስ ይማር ድሬር!! በአመቱ መጨረሻ መምህር ስንገመግም መምህሩ "በእርግጫ ተማሪ ይማታሉ" ሲባሉ "እኔ አላስታውስም" አሉ። የአራዳ ልጅ!! እንዲህ እንዲህ እያለ የእኛ ክፍል አንገቱን ቀና ማድረግ ጀመረ። የፓለቲካው ጉዳይም ተንቀሳቀቀሰ። Z ቀንደኛ የኢህአዴግ ተቃዋሚ ነገር ግን ለብዓዴን አባል የሚመለምል ልጅ ነበር። እኔንም አንድ ግዜ "ለምን አባል አትሆንም ስትመረቅ ስራ ታገኛለህ" ብሎኝ ነበር ። "አንተ ስለምትቀጠር በጓደኝነት ታስቀጥረኛለህ" ብየው ተለያየን። ከእኛ ክፍል 2 ልጆች ብቻ አባል ያልሆንን ስንገኝ ከተለያየ ትምህርት ክፍል የተሰባሰበው የዱርየው ቡድንም እንዲሁ አንዱም አባልነት ውስጥ አልነበሩም። መጨረሻ ላይ አንዱ የክፍል ጓደኛየ "ምን ቸገረህ ዝም ብለህ አባል ሁን" ብሎኝ ስብሰባ እንድገኝ አደረገኝ። ዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ የፖለቲካ ስብሰባ ማድረግ ስለማይቻል ጫካ ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ ተሰበሰብኩ። ግምገማ ተጀመረ።
"አንተ በግ ተራ መቆም ታበዛለህ፣ እገሌ ከእንትና ጋር ተጣልተዋል እና የተጣሉት ደግሞ በዚህ ምክንያት ነው፤ አንተ መንገድ ላይ ሰላም አትለንም" ምናምን የሚሉ የግምገማ ሃሳቦች መምጣት ሲጀምሩ ስብሰባውን አቋርጬ በዚያው ጫካ ገባሁ።(ጫካ ስል ደግሞ ሌላ እንዳይመሥላችሁ። ከጫካው ውስጥ ኳስ የምንጫወትበት ሜዳ ስላለ ነው) ከዚያ ወዲህ የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ሳልሆን እስከ አሁን አለሁ። 2ኛ እና 3ኛ ዓመት ላይ ክበባት ውስጥ መሳተፍ ጀመርኩ። ቆይቶ የመዝናኛና ስነ-ፅሁፍ ክበብ ምክትል ፕሬዝዳንትነት ስልጣን ተሰጠኝ።( ሃሃ ም/ፕሬዝዳንት!!) የግቢው ስልጣን የሃይል ሚዛን ወደ እኛ ክፍል አመራ። የተማሪዎች ህብረት ምክትል ፕሬዝዳንት፣የጂሲ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዝዳንት፣የፀረ ኤድስ ክበብ ምክትል ፕሬዝዳንት፣የመዝናኛና ስነ-ፅሁፍ ክበብ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የጂሲ ኮሚቴ መዝናኛና ስነፅሁፍ ክፍል ተጠሪ የሚባሉት ስልጣኖች ተጠቅልለው እኛ ክፍል መጡ።ተሿሚዎች Gtnet Asrat Yayesew Shimelis Gashaw Eshetu አዲስ መኮንን :: እኔ በመዝናኛና ስነ - ፅሁፍ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ማዕረግ የጂሲ ኮሚቴውን የመዝናኛ ክፍል ተጠሪነት ደርቤ ያዝኩ። ስልጣን ሲመጣ እንዲህ ነው!! ይሄ የሆነው ግን ዱርየነቴን ከተውኩ በኋላ ነው።በእነዚህ አይነት የስልጣን ክፍፍል የሃይል ሚዛኑ ከአንድ ክፍል ወጥቶ ወደ ሸዋ አደላ ተብሎም ብዙ ታማን። የፖለቲካው የሃይል ሚዛን ደግሞ ወደ ጎጃም እና ጎንደር አምርቷል ተባለ። የብአዴንን አባልነት አብዛኛውን ስልጣን እነሱ ይዘውታል ተብሎ ቅሬታ የቀረበበት የምስራቅ ጎጃም ዞን የብአዴን ፅህፈት ቤት ኋላፊ መሰለኝ
"የሸዋ ሰው አትንኩኝ አልነካችሁም ፤ አትድረሱብኝ አልደርስባችሁም ነው። እና እኛ ምን እናድርጋችሁ" አለን ብለው ሢያስቁን ነበር።
እኔ በስልጣን ዘመኔ (ከ2003 -2004) የበደልኩት ወይም የጨቆንኩት ሰው ባይኖርም የስነ ፅሁፍ ምሽት ስናዘጋጅ ተማሪ እየበዛ በመምጣቱ አንድ ቀን አዳራሽ ሞልቶብን በር እንዲዘጋ እና ተማሪ እንዳይገባ አዝዤ ነበር። ያን ግዜ "ተማሪዎችን ስነ-ፅሁፍ ምሽት ላይ ገንዘብ እያስከፈለ አስገባ" ተብሎ ተወራብኝ። የስለላ መረቤን ዘርግቼ ጉዳዩን ሳጣራ በር ላይ የነበሩ ልጆች የተማሪውን መብዛት አይተው የተወሰኑ ተማሪዎችን እያስከፈሉ እንዳስገቧቸው ደረስኩበት። ልጆቹን አድሳለሁ ስል እኔም ሳላድሳቸው እነሱም ለእድሳት ሳይበቁ ተመርቀን ወጣን። ይብላኝ ለቀጠራቸው ተቋም!!
በስልጣን ዘመኔ የሚቆጨኝ ግን የምረቃ መፅሄታችን ላይ የወጣው የስነ-ፅሁፍ ስራ ነው። በጣም ጥሩ ጥሩ የስነ-ፅሁፍ ስራዎችን ገምግመን ካፀደቅን በኋላ ሁለቱን ልጆች ለአርትኦት ስራ አዲስ አበባ ልከናቸው አንደኛው ለፍቅረኛው የፃፈላትን ደብዳቤ የሚመስል ግጥም አትሞበት መጣ።
በስተመጨረሻ ከእኛ ክፍል መንግስትን ክፉኛ ይቃወም የነበረ ልጅ ሃገሩ ገብቶ የወጣት ሊግ ሰብሳቢ ሆኖ አግኚቼው "ምነው?" ብለው
"አብዮታዊ ዲሞክራሲ ተጠምቄያለሁ"ብሎ አለኝ። ምስኪን Z ደግሞ ለብዓዴን አባል ስትመለምል ከርማ መጨረሻ ላይ ሰክሮ ነው አሉ "የወያኔን ዲግሪ ማየት አልፈልግም" ብሎ ግዜያዊ የዲግሪ ወረቀቱን መንገድ ላይ እንደቀደደው ሰምቻለሁ)።
ክንፍፍፍፍ ያለ ፍቅር ያየዘኝም ያን ግዜ ነበር።
"ያሳለፍነው ግዜ ደስታን ያየንበት
ተመልሶ ቢገኝ አሁን ምን አለበት" አለ ጥልሽ!!

No comments:

Post a Comment

Translate

About Me