Search This Blog

Friday 3 June 2016

የመንግስት ለውጥ አይቀሬ በመሆኑ የመሬት የሊዝ ዋጋ
መጨመር አያሳስበኝም


ሰሞኑን ለስራ ጉዳይ ከአዲስ አበባ 130 ኪ.ሜ ርቀት ላይ
ከከተመችው ደብረ ብረሃን ተገዤ ነበር። የከተማዋ ወሬ ሁሉ ስለ
ሊዝ ነው።መሬት ጣራ ነካ፤ እኛ ድሆች መቼም ቤት አይኖረን፤
ከፍተኛው የገንዘብ ፍሰት ባልተማሩ ሰዎች ተይዟል፤ እና ሌላም
ሌላም ጉዳዮች በከተማዋ ይናፈሳል። እኔም አገሬው ይህንን
ያክል በጉዳዩ ላይ ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚያወራው ምን
ተፈጥሮ ነው ብየ ሰዎችን ለማናገር ወ�ሰንኩ። የከተማ
አስተዳደሩ ባወጣው የሊዝ ጨረታ ላይ የተሳተፈችን ሴት
አገኘሁ።"በዚች ከተማ 1ካሬ እስከ 10,100 ብር እየተሸጠ
እንዴት ብለን ነው ቤት ሰርተን መኖር የምንችለው" የሚል ሃሳብ
ሰነዘረች።
የከተማ አስተዳደሩ ከ240 ካሬ ጀምሮ ከዚያ በላይ ስፋት
ያላቸውን ቦታዎች በጨረታ ሸጧል።አንድ ካሬ 10,100 ብር
ድረስ ተሸጧል። 240 ካሬውን ብናሰላው 2ሚሊየን 4መቶ 24ሺ
ብር ይሆናል። ገዢው ቦታውን ሲረከብ 10 ከመቶውን ቅድሚያ
መክፈል ግዴታው ነው። ይሄ ሰው በመጀመሪያ ክፍያ 240,400
ብር ይከፍላል። ከዋናው ዋጋ ላይ የመጀመሪያውን ክፍያ ቀንሰን
ወለዱን ስናሰላው ዋጋው እዚያው ላይ ነው የሚሆነው። ይህም
2,424,000-240,000= =2,181,600 የዚህን 9 ከመቶ ወለድ
ስናስብለት =196,344ይመጣል። ከቀሪ ክፍያችን 2,181,600
ላይ ወለድ 196,344 ስናስብበት =2,377,944 ይሆናል።
ከ2,424,000 ብር ቅድሚያ ክፍያ 250,000 ከፍለም እንኳ
46,056 ብር ብቻ እዳ እንደከፍለን ነው የሚቆጠረው።ሂሳቡን
እናቅልለው።ይሄ ሰው በ40 ዓመት ውስጥ 6,550,945.25 ብር
ወለድ ብቻ ይከፍላል። ክፍያውን በ40 ዓመት እጨርሳለሁ ቢል
በወር 18,697.80 ብር መክፈል አለበት። ቤቱን ሰርቼ አከራይቼ
እከፍላለሁ ቢል እና በ18 ሺ ብር ቢያከራው የራሱ ቤት ሊሆን
የሚችለው ከ 40 አመት በ�ኋላ ነው ማለት ነው። ቅድሚያ
ሁሉንም የመክፈል አቅም ቢኖረው ደግሞ እዚች ከተማ ላይ በ1
ሚሊየን ብር ከ4 መቶ ካሬ በላይ ቦታ ተኩራርቶ ይገዛለታል።
ይሄ ለምን ሆነ፦
ውክልና ወስዶ ቤት ሊገዛ ሲዘዋወር ያገኘሁት ወጣት
ቤተማሪያም ብርሃኑ "ከፍተኛው ገንዘብ ያለው ያልተማረው
የህብረተሰብ ክፍል ላይ በመሆኑ ከኢንቨስትመንት ይልቅ ቦታ
መግዛትን ብቻ ታላሚ ያደረገ ነው"ይላል። አብዛኞቹ ሰዎች
በረጅም ጊዜ ክፍያ ስለሚከፈል ቀላል ነው የሚል እሳቤ እንጂ
ወለዱ ምን ያክል ጣሪያ እንደሚነካ አልገባቸውም። ቤቱን ሰርቼ
ሳጠናቅቅ ምን ያክል ተጠቃሚ እሆናለሁ አይሉም። ለግዜው
እጃቸው ላይ ባለው ብር ቦታ መግዛት እንጂ ብሩን ወደ ሌላ
ብር መቀየር አይታሰባቸውም። በጣም በርካታ ሰው ይህንን
ሂሳብ መስራት አልቻለም። ሌላውና አስቂኙ ነገር ደግሞ
አንዳንድ ሰዎች ጠቅላላ ሂሳቡን አስልተውት ከፍተኛ ገንዘብ
መሆኑን የተረዱ ቢሆንም የመንግስት ለውጥ መምጣቱ
አይቀርም ብለው የሚያስቡ እንዳሉ ያነጋገርኩት ደላላ ሹክ
ብሎኛል።
መንግስት ምን ይጎዳል
ትልቁ ጥያቄ ይሄ ነው። በየከተሞቹ ውስጥ ያሉ ባለሃብቶች
ብራቸውን ቦታ ላይ ሲያውሉት ከተማው ውስጥ የሚኖረው
የገንዘብ ፍሰት በክፍተ��ኛ ሁኔታ ይቀንሳል። የንግድ ተቋማት
ግለሰቦች ያስተዳድሯቸው በሚባልበት �ሰዓት የግለሰቦች
ገንዘብ በመንግስት እጅ ከወደቀ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ይገታሉ።
የግለሰቦች ገንዘብ ሆቴል ሲሰራበት ሰዎች እዚያ ሄደው
ሲመገቡ፤ሆቴሉ ለሰራተ�ኛ ሲከፍል፤ ገንዘቡ ከተማዋ ውስጥ
ሲዘዋወር ጂዲፒው ላይም አወንታዊ ተፅእኖ ያሳድራል።ያለዚያ
ግን ከተሞች እየደቀቁ ይመጣሉ።ለምሳሌ በ40 ዓመት 8ሚሊየን
ብር ለመንግስት ከሚከፍል ይልቅ ገንዘቡን ቢሰራበት እሱም
ከተማዋም የከተማዋ ነዋሪዎችም ይጠቀማሉ። ከዚህ
በተጨማሪም ብሩ ሲሽከረከር እና ግብር ሲከፈልበት እንደ ሃገር
ጥቅሙ ከፍተ�ኛ ነው።
የማህበራዊ ቀውስ
አሁን ላይ የመንግስት ሰራተኞች እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው
ነዋሪዎች ቦታ ገዝተው ቤት ሰርተው መኖር አንችልም ብለው
ደምድመዋል። የእውነትም መንግስት እገዛ ካላደረገላቸው
በ�ስተቀር የማይታሰብ ነው። ሰዎች በኑሯቸው ተስፋ በቆረጡ
ቁጥር ደግሞ ወደ ህገ ወጥነት ተግባር ያመራሉ። በቅርቡ
በአዲስ አበባ .... ያስታውሷል።የቤት ችግር ሲያማርራቸው
ሰዎች በህገ ወጥ መንገድ ባገኙት ቦታ ቤት ሰርተው መኖርን
ይመርጣሉ። ህጋዊ አይደላችሁም በሚል ከመንግስት ጋር
ግጭት ውስጥ ይገባሉ። ይሄ ደግሞ መንግስትን እና ህዝብን
ሆድና ጀርባ ያደርጋል። መወነጃጀሉ እና መወቃቀሱ ይጨምራል

No comments:

Post a Comment

Translate

About Me