Search This Blog

Thursday 2 June 2016

ገድለ እምየ አፄ ምንይልክ የአደዋው ጀግና (እኝህ ቂመኛ ሰው)


ገድለ እምየ አፄ ምንይልክ የአደዋው ጀግና (እኝህ ቂመኛ ሰው)



አፄ ምንይልክ እና ንጉስ ተክለሃይመኖት እምባቦ ላይ ጦርነት አካሂደዋል። የሸዋ ጦር በፈረስ እና በብዛት ነው እንጂ ለተኩስ አልተፈጠረም በሚል ጦርነት ለመግጠም የፈለጉት ንጉስ ተከለ ሃይማኖት የእንዋጋ ምልዕክት በቃል ለአፄ ምንይልክ ላኩ። መልዕክቱን በቃል ያደረጉበት ምክንያት ሰው ይሰማዋልና በግድ እንዋጋለን ብለው ነው።ምንይልክ ነገሩ እውነት ሥላልመሰላቸው መልዕክተኛ ልከው አረጋገጡ። ጠብቀኝ ብለው ላኩም።ጦርነቱ ተጀመረ። እምባቦ ላይ ቀድሞ የሰፈረው የንጉስ ተክልሃይማኖት ጦር የአፄ ምንይልክን ጦር መፈናፈኛ አሳጣው።በኋላ አፄ ምንይልክ ወታደሩን "ተኛ፥ ተኩስ ሳልልህ እንዳትተኩስ" ብለው አዘዙት።(ተለሽለሽ ይሉታል አፍወርቅ ገብረየሱስ) የአፄ ምንይልክን ጥላ መወጠር እና የሰራዊቱን መተኛት አይቶ "ጨርስኳቸው" ያለው የንጉስ ተክለሃይመኖት ጦር ምንይልክን ለመያዝ ተንቀሳቀሰ። ጦሩ ሲቃረብ ምንይልክ ጦራቸውን ተኩስ አሉት። ያ ሁሉ ጀግና አለቀና ንጉስ ተክለሃይማኖትም ቆስለው ተያዙ።ይማሩኝ ብለው እግር ወደቁ።
አፄ ምንይልክ ቂም ሳይዙባቸው "ምንም አላደርግህ ተነስና ሳመኝ" ብለው ዝቅ ብለው አንስተው ተስማሙ።ቁስላቸውንም በንጉስ እጃቸው እንደ ወጌሻ ሆነው አረሩን ፈልፍለው አውጥተው ቁስላቸውን በዶሮ ለባ እያጠቡ አዳኗቸው። ከጦርነቱ በኋላ አፄ ምንይልክ እና ንጉስ ተክለሃይማኖት ሲጨዋወቱ አፄ ምንይልክ ንጉስ ተከለሃይማኖትን "አንተ ጦርነቱን አሸንፈህ ቢሆን ኖሮ ምን ታደርገኝ ነበር?"አሏቸው። "እውነቱን ለመናገር እኔ ድል አድርጌ ቢሆን ኖሮ ወዲያውኑ አስገድልዎ ነበር" አሉና ነገሩ በሳቅ ተደመደመ። በነገራችን ላይ አፄ ቴዋድሮስም ከሸዋው ሃይለመልኮት ጋር ሊዋጉ "ጠብቀኝ ጠብቀኝ" ተባብለው ደብረ ብረሀን ላይ አፄ ቴዎድሮስ ጦራቸውን አሰልፈው ሲጠብቁ የኋይለመለኮትን ሞት በሰሙ ግዜ ከሚቀበሩበት ደብረ በግዕ ድረስ ሄደው ሲቀበሩ ባዩ ግዜ አልቅሰዋል። አያችሁ! ታሪካችን እኮ አሁንም ይብልጠናል። አይ ሰብዓዊነት!!!!!

No comments:

Post a Comment

Translate

About Me