Search This Blog

Thursday 2 June 2016

ሴቶች ለአዳር እንጂ ልትዳር የሚሆን ወንድ የለም፤ ወንዶች ደግሞ ሴት
እንጂ ሚስት የለም እያሉ ነው። ለምን?


በቅርብ እንዲህ ሆነ። ሁለቱ በአጋጣሚ ሰርግ ላይ ይተዋወቃሉ።
ትንሽ ትንሽ ሲሉ እዚያው ሰርግ ቤት ምን አለሽ? ምን አለህ...
ውስጥ ይገቡና ሀብትም ተቁዋጠራሉ። ሁለቱም ያወሩት ሀቅ
የሆነ ህይወታቸውን ነው። ልጅቱዋ በልጁ ንግግር ውስጥ ጉራ
ያለ መስሏታል።እሱም እንዲሁ በአስተሳስብ እኔ እሻላለሁ የሚል
ቅልፄ ልጅቱዋ ላይ ታዝቧል። ሁለቱም ግን ትክክል ናቸው።
ባለህ ነገር መመካት መብት ነው በመንፈሳዊ መልኩ ሲታሰብ
ሌላ ትርጉዋሜ ቢኖረውም። ልጁ በልጅቱዋ ላይ ይሆነ ስሜት
ተሰምቶታል። የሆነ ነገሩዋን ወዶታል። ስልክ ተለዋውጠው እራት
ለመገባበዝ ይቀጣጠራሉ። በማግስቱ ራት ለመብራላት
በተቀጣጠሩበት ቦታ ልጅቱዋ 2 ጉዋደኞቿን ይዛ መጣች።
3ቱንም ጋበዛቸው። አልተከፋም። በ3ኛው ቀንም ቀጠራት ።
ዛሬም ከጉዋደኛቿ ጋር መጣች። ተጋበዙ ሄዱ። በዚህ መካካል
በአስተሳሰብ እኔ እሻላለሁ የምትለውን ልጅ አስተሳሰቡዋን
እየገመታት ነው። ልጅቱዋ በዘበዝኩት ደግ አደረኩ የሚል ስሜት
ውስጥ ነች። እሱ እንዲህ እንደምታስብ እያወቀ ሆን ብሎ
እያደረገው ነው። በሌላ ቀን እራት ጠራት። ዛሬም 3 ሆና
ምጣች። የእሷ አለማፈርን ትተንው የጉዋደኞቿ ድርቅና
ያበሳጫል።ያን ቀን አንድ ነገር አስቡዋል። ራት በልተው
እየጠጡ እያለ ልጁ ሽንት ቤት የሚሄድ መስሎ ትቷቸው ጠፋ።
ቢጠበቅ አይመጣም። ወጪ ለማስወጣት እንጂ ለክፍያ
ያልተዘጋጁት ሰዎች መላ ቅጡ ጠፋቸው። በጣም ደነገጡ።
የልጁ መጥፋት ሳይሆን ያሳሰባቸው የሂሳቡ ያለመከፈል ነው።
ጠበቁት አልመጣም። ደወሉለት አያነሳም።ግራ ገባቸው። ምን
ማድረግ እንዳለባቸው ተመካከሩ። ወንዱ ብቻውን እንዲከፍል
የተፈረደበትን ለ3 አቃታቸው። 2ቱንም ጉዋደኞቿን ይዛ
እየመጣች ሥትበዘብዘው ያላሰበች እንዴት እንዲህ ያደርጋል
ብላ ተናደደች። ለሰከንድ እንኩዋ ችግር ገጥሞትስ ቢሆን ብሎ
ያሰበ አልነበረም። ያላቸው አማራጭ የሞባይል ስልካቸውን
አስይዘው በማግስቱ መጥተው መክፈል ነበር። ለዚህ ደግሞ
ምን ምክንያት ያስብቡ? ከ3 አንዳቸው እንኩዋ እንዴት ብር
ሳይዙ ይወጣሉ መባሉም አሳስቡዋቸዋል። አማራጭ
ስላልነበራቸው አስተናጋጁን ጠርተው ሂሳብ እንዲያስብላቸው
ጠየቁት። 700 ብር ቆጥሩዋል። የተጠቀሙበትን እቃ አስተናጋጁ
አነሳው። ዝም ዝም አሉ። ልጅቱዋ የራሱዋ ጉድ ሰለሆነ ስራ
አስኪያጁን ሄዳ ብር ጥለው እንደሆነ ተናግራ ስልክ
አስቀምጠው መሄድ እንደሚፈልጉ ነግራው ተስማሙ።
ስራ አስኪያጁ አስተናጋጁን ጠርቶ ጉዳዩን ነገረው።
አስተናጋጁም ልጁ ከፍሎ እንደሄደ ነገረው። በዚህ መካከል
ልጅቱዋ ስልክ ስትደውል ልጁ ስልኩን አነሳው። ቀጥታ ስድብ
ጀመረች። ዝም ብሎ ተሰደባላት። ባለጌ ነህ አለችው።
ስትጨርስ ዘጋችበት።
አስተናጋጁ መጥቶ ልጁ ሂሳብ ከፍሎ ነው የሄደው አላቸው።
ደነገጡ፡፡ አስተናጋጁንም እና ከተከፈለ ለምን ቀድመህ
አትናገርም ነበር ብለው ወረዱበት። ምንም አላላቸው።
ተመካክረው ነበርና።
በማግስቱ ደወለችለት። ይቅርታ ጠየቀችው። ብቻዋን
እንድትመጣ ቀጠራት። መጣች።
ዝም ብለሽ አዳምጪኝ አላት። አንቺ በአስተሳሠብ የተሻልኩ ነኝ
አልሽኝ። አስተሳሠብሽን ግን አየሁት። ልጋብዝሽ ስቀጥርሽ
ተንጋግተሽ ከአንዴም ሁለት ሶስቴ መጣሽ። ይህም ይሁን
በቀደም ለምን ሳይከፍል ሄደ ብለሽ ተሳደብሽ። እኔ ብቻያን
የምከፍለው ለ3 ከብዱዋችሁ አረፈ። እሺ እሱም ይሁን ከሰው
እና ከገንዘብ ማን በልጦብሽ ነው ስጠፋ እና በተደጋጋሚ
ደውለሽ ስልክ አላነሳ ስልሽ ምን ሆነህ ነው ብለሽ
ያልጠየቅሽኝ። አይሽ አስተሳሰብሽ እዚህ ድረስ ነው። ብሎ ምሳ
አዞላት ከፍሎ ሊሆድ ሲል አብራው ወጣች። ከዚያ ወዲህ አፍራ
ተወችው።
የጊዜ ጉዳይ ሆኖ ነው መሰለኝ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች
በተቃርኖ ውስጥ ናቸው። ሁለቱም ወገኖች ወደ ትዳር
ከሚወስድ ግንኙነት ይልቅ ኮንትራት የሚመስል ግንኙነት ውስት
ይገባሉ። መወቃቀስ ብቻ። እንዲህ ናት እንዲህ ነው ብቻ።
ለትዳር አይሆንም ለትዳር አትሆንም ብቻ። ሁለቱም ጋር ፍላጎቱ
ኖሮ እንኩዋ ጥሩ ነገርን ከጉዋደኞቻችን ጋር ማውራት ይሳነናል።
እየወደድንው እየወደድናት እንኩዋ መልካም ነገርን ብናወራ
ወደሽዋል ወደሃታል እንዳንባል መደባበቅ። በዚያውም መቃረኑን
መፍጠር። በዚያው በሚውሩ ነገሮች ብቻ መራራቅ።
አንዳንድ ፀሀፉዎች የሚፅፉትም ሆነ ፌስ ቡክ ላይ የሚነገሩ
ነገሮች ይህንን አመላካች ናቸው። እና አሁን እነዚህ ሁለት
ቡድኖች ተቃርኖ ውስጥ ናቸው። በተቃርኖ ውስጥ ግን ትንሽ
ሰዎች ናቸው ሁሉም ሰው አንድ አይደለም የሚሉት። ለምሳሌ
ሴትን ማመን የለብንም ውንዶች ምንም አይመርጡም የሚሉ
ነገሮች ሲነሱ አንዳንዶች ለዚያውም ጥቂቶች ብቻ ናቸው ሁሉም
ወንድ ወይም ሴት አንድ አይደለም የሚሉት። ሌሎቹ ነገሩን
የባሰ ያራግቡታል። እናም እኔ ተቃርኖው እየሰፋ የሄደ
ይመስለኛል። ሴቱም ወንዱም ትዳር ጠፋ ባይ ነው። ከአንድ
በኩል ብቻ ቢሆን የቁጥር አለመመጣጠን ወይም ሌላ እንል
ነበር። ያ ግን አይደለም። እናም ተቃርኖው ያመጣው
ይመስልኛል።

No comments:

Post a Comment

Translate

About Me