Search This Blog

Thursday 2 June 2016

 እርገጤ














እኔ ምን አውቃለሁ
አያ እረገጤ ካሳ ይደፈጥጠኛል ሲወጣ ሲገባ
ለጥበቃ ብለን በሰጠነው ቦቲ ባለበስነው ካባ
እኔ ምን አውቃለሁ
ለስኩዋር ተሰለፍ

 ለዘይት ተሰለፍ
ለዱቄት ተሰልፍ
ለውሸት ሰልፍ ውጣ
ሲያሻው ገንዘብ አምጣ
ይለኛል እረገጤ የሰፈር ጡንቻማው
ደስ ያላለውን ሰው በቴራ 'ሚያስተኛው
እኔ ምን አውቃለሁ
ወንድነቴ ከድቶኝ ይፈታተነኛል
እርገጤ ሲመጣ ሽንቴ ያመልጠኛል
እኔ ምን አውቃለሁ
የመንደር ሰው ሁሉ አንገት የደፋለት
ያ አያ እርገጤ ካሳ አዚም እንዳለበት!
እኔ ምን አውቃለሁ
እግዜር በጥበቡ እርገጤን ካልሻረው
ወይም ደብተራውን ከስር ካልነቀለው
እኔ ምን አውቃለሁ
ነገም ሌላ ቀን ነው
ይልቅስ ፈጣሪ
የድፍጣጬን ጎልበት እርገጤን በእርግጫ ብየው እንድመጣ
ሚስኮል አድርግልኝ ሽርፍራፊ ሰከንድ ስትቀርህ ልትመጣ

No comments:

Post a Comment

Translate

About Me