Search This Blog

Friday 3 June 2016

ሰልፍ፣ ህገወጥ ሰልፍ እና ሠላማዊ ሰልፍ

ሰልፍ፣ ህገወጥ ሰልፍ እና ሠላማዊ ሰልፍ ******ቤተማርያም ብርሃኑ birhanubete200@gmail.com

መንደርደሪያ ትዝታ
(ተማሪ ሆነን ካሳለፍነው በጣም የማልረሳው ግዜ )

..... እሁድ የተጀመረው ብጥብጥ ለሰኞ ተላልፎ ጠዋት ከእንቅልፌ ስነሳ ዩንቨርስቲው በጭስ እና በጩኸት ተደበላልቆ የጦር አውድማ መስሎ ነበር የጠበቀኝ፡፡ (ያው የጦር አውድማ እንዲህ ነው ብዬ ስለምገምት ነው) ለጥቂት ሰዓታት የዘለቀው የተማሪው እና አድማ በታኝ ፖሊስ ፍልሚያ አስገራሚ ነበር፡፡ የተማሪው ታክቲክ በመልሶ ማጥቃት እና 'የጦር ግንባሩን' በመለጠጥ ሲሆን አድማ ብተና ደግሞ በ'ቆረጣ' ነበር፡፡ (ከያዙ በዱላ ሳይቆራርጡ አይለቁም-እንኳንም ዱላ ሆነ እንጂ....) በዚህ ሁኒታ ከአጭር ርቀት እስከ ግማሽ ማራቶን ሲሮጥ - ከአሎሎ እስከ መዶሻ ሲወረወር (ኮብልስቶን ድንጋይ እና ቁርጥራጭ እንጨት)  ቆይቶ ተማሪው በጣም ደከመ፡፡ ( በርግጥ ስፖርት ተማሪዎች ጥሩ ልምምድ የሰሩበት አጋጣሚ እንደነበር አልሸሸጉም) በመጨረሻ ተማሪው  ታክቲኩን ወደ ጎሪላ ዋር ፌር ሲቀይር ለአድማ በታኞች አልመች አለ፡፡ እናም በፖሊስ ሰፈር ዘዴ ተቀየሰ- በድምፅ ማጉያ ተማሪው ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ሰልፍ ወጥቶ እንዲገልፅ ተጠየቀ፡፡ ተሜም ሳያመነታ ከዩኒቨርስቲው ወደ ከተማ ተመመ፡፡
ፖሊስ ሆዬ የልቧን በልቧ አድርጋ ያላንዳች ችግር ግቢውን ያዘች፡፡ ተማሪው ሰልፉን በመፈክርና እና በኡኡታ አጅቦ ጉዞውን ወደ ተ/ሃይማኖት አደባባይ አደረገ፡፡ በግዜው በጣም የገረመኝ ብጥብጡ የተነሳው በምግብ የነበረ ቢሆንም ቀስ በቀስ ፖለቲካዊ ይዘት ማሳየት ጀመረ፡፡ ይሄኔ ነው እንግዲህ እነ አጅሬ  'ደሞ ባይኔ መጣህ?!' ብለው መዝፈን የጀመሩት፡፡ ዘፍነውም አልቀሩ በአስደናቂ ፍጥነት ዙርያችንን ከበው የአስለቃሽ ጭስና የጥይት ናዳ ለቀቁብን (አይዟችሁ ጥይቱ ወደሰማይ ነው!) ከዚያማ ምኑ ይወራል? በቃ አከባቢው ቀውጢ ሆነ! ዷዷዷ... ኳኳ..ፒሽው! ያዘው! ያዘው! እንዳያመልጥ! ሩጫ...ጩኸት ... መውደቅ...መነሳት.... ለቅሶ... ዋይታ  .... ዱላ... ሁሉም በአንድ ግዜ!..
መሮጥ ስጀምር ወደቅኩ...ስነሳም ወደቅኩ ...እንደገናም ስሞክር አልሆነም፡፡ ወደእግሬ ሳይ አንድ በደረቱ የተኛ ተማሪ ጣቱ የእኔ ጫማ ማሠሪያ ውስጥ ገብቷል... (ያኔ ስኒከር ጫማ ማሰሪያውን በቄንጥ አስረን ወደውጪ ነበር የምናደርገው) እኔ እግሬን ስጎትት እርሱ በጥርሱ ለመበጠስ ሲታገል...አሁንም ስጎትተው እርሱ ወደ ጥርሱ አልደርስ ብሎት ሲንፏቀቅ... ሲገርም!..... ዝንትአለም የሚመስል ቅፅበት!
ዞሮዞሮ በጫማ ክር መውደቄ ጀርባዬ ላይ ካረፉት ዱላዎች ጋር ተደምሮ በፖሊስ ለመያዝ አበቁኝ፡፡ ታሰርኩ.....ይቀጥላል

No comments:

Post a Comment

Translate

About Me