Search This Blog

Friday 3 June 2016

ሌብነቱ ቅዱስ?

የእነ ጃዋር ቡድን ቀጣዩን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና
ይወስን ይሆን? ሌብነቱስ ቅዱስ?


እንደሚታወቀው መጀመሪያ ሊሰጥ የነበረው የከፍተኛ ትምህርት
መግቢያ ፈተና በሁለት ፈተናዎች ተሰርቆ መውጣት ምክንያት
ግንቦት 22 እንዲቋረጥ ተደርጓል። ጉዳዩ በመገናኘ ብዙሃን
ከፍተኛ ትኩረት አግኝቶ ነበር። በእርግጥ መንግስት በዚህ አመት
ሽንቁሩ በዝቶበታል። መግለጫዎች ሁሉ ድንብርብራቸው የወጡ
ነበሩ። ፕረስ ቲቪ ተሳስቶ "አይ ኤስ 16 ኢትዮጵያውያንን ድጋሚ
አረደ" ብሎ መዘገቡ ምንግስትን አስቸኩሎ ድርጊቱን
እንዲያምን አድርጎ አሳተው። በእርግጥ ከአመት በፊት በአይ
ኤስ የታሩዱት ዜጎቻችንን "ገና በማጣራት ላይ ነን" የሚል
መግለጫ አስጥቶት በብዙዎች ጥርስ ውስጥ ከትቶት ነበር።
ከዚህ ለማምለጥ ይመስላል ለዚህ መግለጫ የቸኮለው።
77ቢሊየን ብር በጀት የተበጀተለት የስኳር ኮርፖሬሽን ውድቀት
ገጠመው መባሉ ሌላው ሽንቁር ነበር። 5 የስኳር ፈብሪካ ሊገነባ
ታስቦ አንድም ስኳር ፋብሪካ ተጠናቅቆ ወደ ስራ ባለመግባቱ
አቧራ ተነሳ። ተጠናቆ ስራ ጀመረ የተባለውም ቆመ። 77ቢሊየን
ብር ገደል ገባ ተባል። የወሬው ዱላ ኮንትራክተሩ ሜቴክ ላይ
አረፈ። በኢቢሲ ለሜቴክ ማገገሚያ የሚሆን ዶክመንተሪ ተሰራ።
ግለቱ ሳይበርድ 89 ኮንዶሙኒየም ጠፋ የተባለው የኦዲት
ሪፖርት ሌላ ግርግር ፈጠረ። ምን አይነት ጅብ መጣብን ተባለ።
ከሳምንት በኋላ አልጠፉም የሚል ማስተባበያ ተሰጠ። ሚዲያው
በተለይም ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያው ቀኑን የሚያደምቅበት
ወሬ ለጉድ ሆነለት። በዚህ ግርግር ላይ በኦሮምያ አመፅ
ምክንያት ፈተና ተሰረቀ ተባለ። መንግስት ንዝህላልነትን አበዛ
የሚል ወቀሳ ተሰነዘረ። ከፈተናው ቀደም ብሎ የትምህርት
ምኒስትር "ፈተና ተሰርቆ ወጥቷል የሚለው አሉባልታ ከእውነት
የራቀ ነው" የሚል መግለጫ ሰጠ። ማህበራዊ ድህረ ገፆች
አሉባልታ የተባለውን ጉዳይ ገፍተውበት ጭራሽ ፈተናውን
በተኑት። መግለጫውም አሉባልታ ባለበት አንደበቱ ፈተናውን
መሰረዙን ተናገረ። ከፈተናው መሰረዝ በኋላ ደግሞ ሌላ ግርግር
ተነ�ሳ። መንግስት ፈተናው ከሰኔ 27 ጀምሮ ይሰጣል አለ።
ፈተናውን ሰርቃናል ያለው አካል ደግሞ ቀኑ የረመዳን በዓል
በመሆኑ መቀየር አለበት በሚል የትምህርት ምኒስቴር ውክልና
የሰጠው ይመስል መግለጫ አወጣ። መግለጫው በእነ ጃዋር
መሀመድ የሚመራ ነው። የፈተና መስጫው ቀን ካልተቀየረ
ድጋሚ ፈተናውን ሰርቀን በሃገር ንብረት ላይ ኪሳራ እናደርሳለን
እያሉ ነው። በነገራችን ላይ ፈተናው ረመዳን ላይ በመግጠሙ
ምክንያት "እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም" ያለም ታወቂ ሰው አለ።
በመሰረቱ ሌብነት ወንጅል ነው። ነገር ግን ኮንዶሙኒየም
ከነነፍሱ በሚጠፋባት ሃገር 'ጥያቄያችንን መንግስት
አልሰማንም' ብሎ ፈተና መስረቅ ግን ሰለማዊ ተቃውሞ እና
ፅድቅም ሊሆን ይችላል። እንደሚታወቀው ኦሮምያ ለ5 ወር
ያክል በተቃውሞ የከረመ ክልል ነው። መንግስት ይህንን ታሳቢ
በማድረግ 'ትምህርታቸውን ያልተከታተሉ አሉ' በሚል እሳቤ
ፈተና የተራዘመላቸው ትምህርት ቤቶች አሉ። የሆነው ሆኖ
ፈተናው ከሰኔ 27 ጀምሮ ይሰጣል ተብሏል።አሁን ያለው
ተቃውሞ ቀኑ የረመዳን በዓል ስለሆነ የሙስሊሞችን መብት
ተጋፋ የሚል አጀንዳ ይዟል። በመሰረቱ ይሄ ሲሰራበት የኖረ
አሰራር ነው። በዓሉን ዘልሎ ፈተና መስጠት ይቻላል። ነገር ግን
ሰዎች ጉዳዩን ፅንፍ አስይዘውታል። ይህንን ፅንፍ ተከትሎ
መንግስት የፈተናውን ቀን ሊያራዝም ይችላል ወይ? ይሄ
የማይታሰብ ነገር ነው። ከሆነም መንግስት በውክልና ነውይ
የሚሰራው የሚል ትችት ይደርስበታል። ተቃዋሚዎች የፈተናን
ግዜ መወሰን ከቻሉ መንግስት ስራውን አቁሟልና ለሚሰራ
ቦታውን እንዲለቅም በዚያው መጥየቃቸው አይቀርም።
እንደፎከሩት ፈተናውን ሰርቀው ማውጣት ከቻሉ የመንግስትንም
ወንበር ለመስረቅ ምንም የሚያግዳቸው ነገር የለም ማለት
ነው። ምናልባት መንግስት ጫናው እየበረታበት ከመጣ ህትመት
ስለዘገየብኝ በሚል ሰበብ የፈተናውን ቀን ሊያራዝም ይችል
ይሆናል። ስልታዊ ማፈግፈግ! ይቺም ታዲያ ከተቃዋሚ ጥርስ
አታወጣም።እልህ መጋባቱ የሚቀጥል ከሆነ ግን የሚጎዳው
ያው የፈረደበት የድሃ ልጅ ነው። ልጄ ተፈትኖ ክረምትን
ለዩኒቨርስቲ መጓጓዣ የሚሆን ፍርንክ ይሸቅላል ብሎ የሚያስብ
ወላጅ፤ ይሄም ሳይሆን ይባስ ብሎ በድሃ አቅሙ ተጨማሪ ወጪ
እያወጣ ነው። ልጆቻቸውን ከተማ ልከው የሚያስተምሩ በርካቶች
ናቸው። ፈተና ለ1 ወር ሲራዘም የአንድ ወር የቤት ኪራ የአንድ
ወር ቀለብ አብሮ ይጨምራል።"ልጄ መቼ ፈተናውን
ይጨርስልኝ" ሲል ለነበረ ወላጅ አንድ ወር ማጥ ነው።
እንደተባለው የክልሉ ነዋሪዎች ልጆቻችን በግርግሩ ሳቢያ
ስላልተማሩ ፈተናው ይራዘምልን ብለው መንግስት ደግሞ ጆሮ
ዳባ ልበስ ብሎ ከሆነ ትልቁ ጥፋት የራሱ የመንግስት ይሆንና
ድርጊቱ ወይም የፈተና ስርቆቱ ሌብነት ይሆናል መጠሪያው
ደግሞ ቅዱስ ሌብነት ተብሎ ይጠራል። ከዚህ በተቃራኒው
የኦሮሞ ተማሪዎችን ለመጥቀም ብቻ ታስቦ ከሆነ ግን የሞኝ
ስራ ነው። እልም ያለ ሌብነትም ነው። ያልለፉበትን እውቀት
ወይም ሀብት አንደመሻት ነው። ትውልድን መግደል ነው። የእስከ
አሁኑ ድርጊት መንግስት ላይ እምነትን አሳጥቷል። በተለይ
የ10ኛ ክፍል ፈተና ተሰርቋል የሚል ወሬ ሲወራ ስለነበር
ብዙዎች "ላለመሰረቁ ምንም ማረጋገጫ የለንም" ብለዋል።
ሰዎች መንግስትን ሁል ግዜ በጥርጣሬ እንዲያዩት ያደርጋል።
የሆነው ሆኖ የፈተናው ግዜ ከተቀየረ እነ ጃዋርን ገብታችሁ
አስተዳድሩን የሚል ሰው ይበዛል።

No comments:

Post a Comment

Translate

About Me