Search This Blog

Thursday 2 June 2016

ሌላው ቀርቶ የሃሳብም ለማኞች ነን

ሌላው ቀርቶ የሃሳብም ለማኞች ነን።(በብሄር የተተበተባችሁ
ይቅርባችሁ አታንብቡት)

@@@@@@@@@@@@
በአንድ ወቅት በአንድ ትልቅ የመንግስት ስብሰባ ላይ መድረክ
መሪው አንዲት ቃል ጣል ያደርግና ተሰብሳቢውን በሳቅ
ይጨርሰዋል። ስብስባው ሰልችቷቸው የነበሩ ወጣቶች ከሁዋላ
ቁጭ ብለው ስልካቸውን ይጎረጉራሉ። ከተዘፈቁበት አለም
ውስጥ የነቁት በአዳራሹ ሰው ሳቅ ነበር። የሳቁበት ነገር ግራ
ገብቷቸው ዞር ዞር ይሉና ከፊት ለፊታቸው በሳቅ እንባውም ጠብ
የሚያደርግን ወጣት ይጠዩቁታል። "ሰውየው ምን ብሎ ነው
እንዲህ የሳቃችሁት?" ይሉታል። ልጁ እንባውን እየጠራረገ
"እኔም አልሰማሁም" ብሎ መለሰላቸው።
ልመና ድህነትን ከማወቅ የሚመጣ ነው። ይህንንም የማያውቅ
ድሃ ለጉድ ነው። ለማኝነቱን አውቆ ለልመናን ያለመዘጋጀት አንዱ
ዜሮነት። ልመና መውጣት ልመናን ካለማወቅ የተሻለ ነው ማለት
ነው። ቢያንስ ለመብላት እየለመንን ስለሆነ እርምጃ እየወሰድን
ነው። ከድህነት የባሰ ድህነት ደግሞ የአስተሳሰብ ድህነት ነው።
ይሄ ከድህነት አልፎ ወረርሽኝ ነው። በተለይ ልንላቀቀው
የማንፈልግ ከሆነ ከወረርሽኝ ይከፋል። የአስተሳሰብ ድህነት
ከተለያዩ ነገሮች ይመነጫል። አንድ ነገር ላይ ሙዝዝ ብሎ ወይ
አይለወጥ ወይ ሰው እንዲለወጥ እድል የማይሰጥ በየቤቱ ቤት
ይቁጥረው። ሃሳቡን አወሳሰብኩት መሰለኝ። ግልፅ ላድርገው።
አንዳንድ ሰዎች ለምሳሌ ባለስልጣናት ከስልጣናቸው ወንበር
ላይ ሆነው ገና ለገና መድረክ አገኘን ወይም ተፈቀደልን ብለው
ከማህበረሰቡ ንቃተ ህሊና በታች ወርደው ስናገኛቸው፤ አየር
ሰዓቱን ለመሙላት ሲል ብቻ የሆነ ያለሆነ ነገር ከሚቀባጥር
ጋዜጠኛ ምን ለያቸው። ባለመድረኩ ድምፅ ማጉያው ቢናገርለት
፣ ባለ አየር ሰዓቱ ደግሞ ምንም ስሜት የማይሰጥ ጫጫታ
ቢሄድበት አይሻልምን? አሁንም ነገሩን አወሳሰብኩት። ይህንን
ያደረኩት የሃሳብ ድኩማኖች እንዳይጨፍሩብኝ ነገሩን
ላወሳስበው ፈልጌ ነው። ሚዛናዊ ሰዎች ሃሳቡን መዝዘው
በአንድምታ ያስቀምጡታል። የሃሳብ ህመምተኞቹ ግን ነገር
ለመጠምዘዝ እንኳ እንዳይመቻቸው ይሁን። ሰው የተፈጠረው
ነፃ ሆኖ ነው። ይልቁንም ራቁቱን። ሰው የተባለው ፍጡር ግን
በሄደበት ሁሉ ግራ እንዲገባው ህግጋትን ደንግጎ በደነገገው
ህግ መዓቀፍ ውስጥ እንዲሽከረከር አደረገው። መሪውም
ተመሪውም በዚያ ምህዋር ውስጥ እኩል ማለፍ ቢችል መልካም
ነበር። ችግሩ ለእንዱ ሁል ግዜ ውድቀትን ሰጪ ይልቁንም
ልጓም ሲሆን ለእንዱ ደግሞ መደላድልን ፈጣሪ ሆነ። ሰው
የተባለው የተረገመ ፍጡር የስልጣን መደላድሉን ለመዘርጋት
የሚመራውን ህዝብ ክፍልፍሉን ያወጣዋል። ሲፈልግ በአካባቢ
፣ሲፈልግ በዘር፣ ሲፈልግ ደግሞ በክላስ። በዚህ ውስጥ መሪው
ለአመራር ባስቀመጠው ስልት ውስጥ ተመሪው ዙሩን ያከርና
ቡድናዊነት ውስጥ ይዘፈቃል። ለዚያውም ፅንፍ የያዘ
ቡድናዊነት።ይህንን ግዜ ነው የሰው እንስሳዊ ባህሪ
የሚንፀባረቀው። ሰው ደግሞ ሰው ነው ልንለው የምንችለው
ራሱን ችሎ በሁለት እግሮቹ መቆም ሲችል ብቻ ነው።ራሱን
በራሱ ሃሳብ መግራት ሲችል እና ከቡድናዊነት ነፃ ሲሆን።
ካለበለዚያ ከእንስሳት በምን ይለያል? በጎች ሲደነብሩ መቆምያ
እንደሌላቸው ሁሉ እሱ ያለበት ቡድን ሲደንብር የሚያረጋጋው
ከጠፋ ከበጎቹ በምን ይለያል? አንዳንድ ቦታ ላይ ስብሰባ ውስጥ
በድምፅ ብቻ መወሰን ያለባቸው ውሳኔዎችን ለመወሰን እጅ
አውጡ ሲባል ዞር ዞር ብለው ማን እናዳወጣ አረጋግጠው
እጅ እንደሚያወጡ ሰዎች አይነት። እኔ እንዲሆንልኝ
የምፈልገውን ነገር ራሴ ብቻ ነኝ መወሰን ያለብኝ። ወደ
ቡድናዊነት እንመለስ።
በቡድን አስተሳሰብ ውስጥ መግባት ደመ ነፍሳዊ መሆን ነው።
የራሱን ቡድን አጥብቆ በወደደ ቁጥር ሌሎችን የሚያይበት
መነፅሩ ይሰበራል፣አይኑም ይታወራል። የራሱን ቡድን መምራት
ውስጥ ካለ አንድ ሰው ጋር ያወዳድርና ራሱን ትልቅ አገልግል
ውስጥ ያስቀምጠዋል። አገልግሉን ቁጭ ብሎ ይሰቅለዋል።ቆሞ
ግን ለማውረድ ይቸግረዋል። የአስተሳሰብ ድሆች ባንሆን ግን
እዚህ ውስጥ አንገባም። የአሰተሳሰብ ድህነታችንን ብናውቅ
ደግሞ ቡድናዊነትን በአገልግል ከትተን አርቀን አንሰቅለውም
ነበር።ከበደ እንዲወድደኝ ብየ ሃጎስን አላጥላላም። ጫላ
ስልጣኑ እንዲረዝም ብየ ከበደ እና ሃጎስን አላቂያቂምም።
መሪው ሚስተር ኤክስ ይህንን አድርግ ቢለኝ ሌሎች የታዘዙበትን
መንገድ ተገላምጬ አላይም። ራሴ እወስናለሁ። ይልቁንም
ጫላን ከበደን እና ሃጎስን በፍቅር እንዲኖሩ እስብካለሁ።
እነዚህን 3ቱን ለማቀያየም ሃሳብ ያመጣው ሰው ሃሳብ
የማመንጨት ችግር የለበትም። ይልቁንም ለእድሜ ማራዘሚያ
የተፈጠረች ሃሳብ ስለሆነች ድንቅ ነው። ከሃሳቡ ስር ያለው እና
ነገ ተነቅሎ የሚጣለው አራሙቻው የሃሳብ ድኩማን ታዛዥነቱ
ያበሳጫል። ነገ እነዚህ 3 ሰዎች ውስጥ መግባቱን፤ በተፈለገ
ግዜ ተነቅሎ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ መጣሉን አያስብም። ያ
ነው የ ሃሳብ ድርቀት ወረርሽኝ። የሃሳብ ድህነት። ከድህነት
የከፋው ድህነት።

No comments:

Post a Comment

Translate

About Me