Search This Blog

Thursday 2 June 2016

የውሃ ቀን ትዝታዎቹ እና መዘዙ

የውሃ ቀን ትዝታዎቹ እና መዘዙ

የኒቨርስቲ ውስጥ በርካታ ቀናት ይከበራሉ። color day,water day,oldis day,culture day ...። እኛ እነዚህን ቀናት ብዙዎቹን አክብረናል። የማይረሳ ትዝታ ያላት ታዲያ የውሃ ቀን ነበረች። ቁኑ እሁድ ቀን ነበር የውሃ ቀንን ያከበርንበት 2004 ዓ.ም። የጂሲ ኮሜቴ ውስጥ የመዝናኛውን ክፍል እንድመራ የተመረጥኩት እኔ ነበርኩ። በዋዜማው የዩኒቨርስቲውን አመራሮች ቀኑን እንድናከብር ፍቃድ እንዲሰጡን ጠይቀን ቅር እያላቸውም ቢሆን ፈቀዱልን። እናም እሁድ ቀን ዝግጅቱ መከበር ጀመረ። ጠዋት ላይ ምንም እንቅስቃሴ አልነበረም።4 ሰዓት አካባቢ ለበዓሉ ድምቀት ውሃ መረጫጨት ተጀመረ።ለተወሰኑ ደቂቃዎች ውሃ ነበር። ትንሽ ቆይተው ውሃውን ዘጉብን። በውሃ መረጫጨቱ የተወሰወሰው ጂሲ የውሃ የመረጫጨት አምሮቱ ቢቆረጥ በዩኒቨርሲተው የቆሻሻ ትቦ በሚወርደው ውሃ ግቢውን ቀውጢ አደረጉት።ያን ቀን ያጠፋንው ጥፋት ቢኖር ቀኑ እንደሚከበር ስናሳውቅ ሰአቱን እና የመረጫጫ ክልሉን ያለመወሰናችን ነው።በዚህ ምክንያት መምህራኖችም አሳፋሪ በሆነ መልኩ ውሃ ተረጭተዋል።ያ ባይሆን ጥሩ ነበር።
የሆነው ሆኖ ውሃ ለምን ተዘጋብን በሚል እልህ በቆሻሻ ውሃ መረጫጨቱ ቀጠለ። ውሃ መረጫጨት አንፈልግም የምን መጃጃል ነው ብለው ሲሉ የነበሩ ሁሉ እንድ ባልዲ ውሃ ሲደፋባቸው እነሱ ብሰው ቁጭ አሉ። በተለይ 3ኛ አመት የህግ ተማሪዎች(2004 ላይ 3 ኛ አመት የነበሩ)ማናባቱ ነው የሚረጨን ብለው ቀኑን ሲያጣጥሉ ቆዩና የተወሰነ ባልዲ ውሃ ሲፈስባቸው ከተመራቂዎቹ ብስው አረፉት። በግ ተራ አካባቢ ውሃ እንደ ልብ ስለነበር ግርግሩ እዚያ ከፍተኛ ሆነ። እርስ በእርስ መረጫጨቱ ቀረና ወደ ቡድን ተቀየረ። ሴት እና ወንድ በሚል። አሁን ቀኑ እየሞቀ ሄደ ወንዶች ወደ ሴቶች ዶርም እንዳይገቡ መከላከል ላይ ቆመን ከወንዶችም ከሴቶችም የሚረጭ ውሃ እላያችን ላይ አለቀ።ቆይቶ ሁለቱንም መቁዋቁዋም ሲያቅተን ጥጋችንን ያዝን። ወንዶችም ሴቶችም እልህ ውስጥ ገብተው በዚያ በቆሸሸ ውሃ እንዲሁ ስንራጭ ምሳ ሰዓት ደረሰ። ያን ቀን ብዙ ወንዶች በዚች ሰበብ ሴቶች ዶርም ገብተው ጉብኝት አድርገዋል። በግ ተራ አካባቢ የነበሩ የሴቶች ማደረያ ህንፃዎች ጭቃ በጭቃ ሆነዋል። የሁለቱ ፆታዎች መረጫጨት ገመድ ጉተታ ይመስል ነበር። ወንዶች ውሃ ይዘው ወደ ሴቶች ሲተሙ ሴቶች ሽሽታቸውን ይይዛሉ በተቃራኒው ሴቶች ውሃ ይዘው ሲመለሱ ወንዶች ተራቸውን ወደ ሁዋላቸው ይመለሳሉ። ዥዋ ዥዌ የሚጫወቱም ይመስል ነበር። ምሳ ሰዓት ላይ ያ በፊት ለመስቀል(ቀድሞ ለመብላት) የሚሯሯጥ ተማሪ ምግብ መኖሩንም ረሳው።ያንን በውሃ የተወሰወሰ ተማሪ መበተን አቃተን። ከተወሰነ ቆይታ በሁዋላ መረጫጨ ቱ ቆመና ጭፈራ ነገር ተጀመረ። ሰዓቱ ወደ 7 ሰአት ተጠጋ። ይህንን ግዜ ነው ተማሪው ካፌ ተዘግቶ ፆሙን ላለመዋል ወደ ምሳ የሄደው። የሆነው ሆኖ ቀኑ ተማሪው እርስ በእርሱ የበለጠ እንዲተዋወቅ አደረገው። በተለይ የወንዶች እና የሴቶች ጎራ መለየቱ ሴቶች ለሴቶች ጋር ወንዶች ከወንዶች ጋር የበለጠ ህብረት ፈጠሩ። ወደ ማታ 10 ሰዓት ላይ ይሄ ህብረት መዘዝ ይዞ መጣ።
ሀሙስ ቀን እራት ስጋ በመዘለሉ ለእሁድ ቀን ተቀይሯል። 10 ሰዓት ስጋ ወጥ ለመብላት የተሰለፈው ተማሪ ዛሬ ስጋ የለም በመባሉ አንበላም የሚል ግርግር ተፈጠረ። እኔ ያገኘሁትን እበላለሁ ብሎ ወደ ካፌ ያመራ ተማሪ የድንጋይ ናዳ ይወርድበት ጀመረ። በዚህ ሰበብ ግቢው ብጥብጡ ወጣ። የምግብ ቤት ሃላፊዎች እና አመራሮች ነገሩን ቀጥታ ወደ ውሃ ቀን አመጡት። የተበጠበጠው በእነሱ ምክንያት ነው በሚል። ግን አልነበረም። ራሳቸውን ከተጠያቂነት ለመውጣት ብቻ ያመጡት ተራ ምክንያት ነበር። ረብሻው ቀጥሎ ፌደራል ፖሊሶች ወደ ግቢው ሲገቡ ነገሩ የባሰ ለየለት። ድንጋይ መወራወር ተጀመረ። ቀኑ መሸ እና ለአይን መያዝ ጀመረ። ያን ግዜ ውጭ ምሳ ለመብላት ከዶርም ስወጣ ተያዝኩ። ምንም ማድረግ አልቻልኩም። ታሰርኩ። 4 ልጆች ተጨመሩ እና 5 ሆነን ሽቤ ገባን። የሚገርመው ዝም ብለው እንጂ በምክንያት የገባ አልነበረም። ከዚያ በሁዋላ የሆነውን ማየት አልቻልኩም። የሆነው ሆኖ በማግስቱ 300 ተማሪዎች ተቀላቀሉን። ያን ቀን የመጡት ግን ቀንደኛ ቀንደኛዎቹ ናቸው። 305 ተማሪ አንድ አዳራሽ ውስጥ። ያን ቀን ጨዋታው ደርቶ ዋለ። ከ300 ዎቹ ውስጥ ተረት ያዘንቡልን ጀመር። በተለይ እንዱ ጉዋደኛችን አንዲት ሴት አለች ብሎ የነገረን ፈጠራ ሳትሆን አትቀረም ታስፈግጋለች። "አንዲት ተማሪ ከውጭ ወደ ዩኒቨርሥቲው ግቢ ስትገባ ግቢውን አሸተተችው" አለን። ከዚያ " ፓ ይሄ ግቢ ዛሬ ወንድ ወንድ ሸተተ" አለች ብሎ አጫወተን። ያን ቀን የተወሩ ቀልዶች ብዙ አንድምታ የነበራቸው ናቸው። ለማንኛውም በ3ተኛው ቀን ብዙዎቻችን ወደ ግቢያችን ተመለስን። በጣም አስቂው ነገር ግን ለ1 ሳምንት ተማሪው በሙሉ ትምህርት አንማርም ብሎ ሸፈተ። ሽፍትነቱ ደግሞ ከተማ መዋል እና ምሳ እና እራት ላይ ለመብላት ወደ ግቢ መግባት ነበር። 6 ሰዓት ላይ ከከተማ ተሰልፋችሁ ግቡ የተባለ ይመስል ቀጥ ብለው ወደ ካፌ ይገባሉ። ምሳ በልተው ተመልሰው ወደ ከተማ ይሄዳሉ። ያ ትዕይንት በጣም ያዝናናኝ ነበር።
ብዙ ነገር አለበት።ከ300ዎቹ አንዳችሁ ጨምሩበት።

1 comment:

Translate

About Me