Search This Blog

Thursday 2 June 2016

የብዓዴንን እና የህወሀትን ደጋፊዎችን ባጅ ገልጠን ስናየው

የብዓዴንን እና የህወሀትን ደጋፊዎችን ባጅ ገልጠን ስናየው
(ባጁን መግለጥ ከአሉላ ሰለሞን ነው የምንጀምረው)
የብዓዴን ደጋፊዎች ህወሃቶችን
"በጨው ደንደንስ በርበሬ ይወደስ" እያሉ ሲሏቸው ሰማን አራት
ነጥብ
ህወሀቶች ብአዴኖችን
"ዝሆንና አይጥ በድልድይ ሲሻገሩ አይጥ ድልድዩ ሲነቃነቅ አይታ
'ዝሆንየ ነቀነቅንው አይደል?'አለች አሉ" ብለው የተሻለ ተረት
እየተረቱባቸው ነው።
የሁለቱም ተቃዋሚዎች ደግሞ
"ድሮ ሁለት የሰፈር አለቆች ነበሩ።አንድ ቀን ለአደን ጫካ
ሲወርዱ ነብር እና አውራሪስ ተጣልተው ድክመው ያገኟቸዋል።
ያንን የደከመ ነብር ይገድሉና ተሽክመው ከጫካው ይወጣሉ።
መጀመሪያ የተሸከመው ሰው ሁለተኛውን እባክህ ሽክሙን
አግዘኝ ይለዋል። አይ ትከሻየን ስላመመኝ ትንሽ ወደ መንደር
ጠጋ አድርግልኝ ይለዋል። ወደ መንደር ሲቃረቡ በል አምጣ
ላግዝህ ሲለው አሁን ትከሻህን ተሻለህ ወይ ይለዋል።አዎ አሁን
መሸከም እችላለሁ ቢለው ነገሩ ገብቶት ቂም ይቁዋጥርና
ይሰጠዋል። የመንደሩ ሰው ነብር ገዳዮችን በአጀብ ተቀበላቸው።
'ነብር ገዳዮች' ተብለው ተሞካሹ። ስጋው ተጠብሶ ገዳይ
እንዲቀምስ ሲደረግ ሁለቱም እኩል ብድግ ይላሉ። ቅድሚያ
ለአንዱ መታደል ስለነበረበት እኔ ነኝ እኔ ነኝ በሚል ፀብ
ተፈጠረ። ሁለቱም በያዙት ጩቤ ተጋደሉ። ቀብራቸው ላይም
'መቃብር ቆፍረው እውነትን ሊቀብሩ
በወደቀ ነብር እኩል ተቀበሩ' ተብሎ ተፃፈ አሉ።" ብለው
እየተረቱ ነው።(የሁለቱም ወገኖች የይስሙላ የእንኩዋን
አደረሳችሁ መልዕክት ግን ተመችታኛለች)
እኛ
የታሪክ ተሻሚዎቹን ባጅ እያገላበጥን አየን። ግማሹ እንደነ
ሪፖርተሩ ፀሀፊ ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው እንዲሉ ቦታው ላይ
የነበሩቱ ታሪኩን እየነገሩት ''ብአዴኖች አያቶቻቸውን መሰሉ''
በማለት ጥራዝ ነጠቅ ፅሁፍ ፅፎ አስነበበን። ፀሀፊው በእነሱ
አገላለፅ በትምክህት እና በማንአለብኝነት ቀጥተኛ ስድብ ነው
የፃፈው። ብዓዴን ማን ያውጋ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ እንዲሉ
የጦር ሜዳ ውሉውን ቦታው ላይ በነበሩ ሰዎች ሲነግረን ነበር።
ህወሃትም ባለፈው ነግሮናል። የህወሃት ልደት ግዜ መቀሌ ላይ
በአሉ ሲከበር "ምነው እነዚህ ሰዎች ድሉ የእኛ ብቻ ነው አሉ?
ኢህዲን አይደለ እንዴ ሰው ያደረጋቸው? ብሎኛል። በአንድ እናት
ድርጅት ከታቀፈ ፖለቲካ ውስጥ እንዲህ ያለ የታሪክ ሽሚያ
መፍጠር አደጋ አለው ብላለች አዛሉ። እኔ የምለው፦ ታሪክን
ተሻማንው አልተሻማንው ታሪክ ራሱ ይናገር የለም ወይ? ምን
ይልክን ያ ሁሉ መደዴ ሲሰድባቸው እኮ የባሰ እምየ የሚላቸው
በዛና እርፍ አለ። በቃ ታሪክ እንደዚህ ነው። ራሱ
ይናገራል።ህዝቡ ራሱ ታሪክም ታሪክ ነጋሪም ነው። ለማንኛውም
እኛ ሁለቱንም በፍትሃዊነት እና ሚዛናዊነት ሰማንና ታሪኩ
የሁለቱም ነው አለን። አዲስ አበባ ተቀምጠው ቦታውን አገኘን
ብለው ታሪክን በማጠልሸት ተጠምደው የሚፅፉ ያጠለሹትን
ታሪክ እንደምሳሌ በማንሳት ሰው ያለመሆናቸውን ምስጢር
በኢህአዴግ ጉያ ተሸጉጠው እያሳዩን ነው። ታግለን አታገልን
የሚል ድርጅት፦ ደጋፊዎቹ በታሪክ ንጥቂያ ውስጥ ሲገቡ
ገለልተኛ ሆኖ ለሚያይ ሰው ስሜቱ ምናባዊነት ድራማ
እንደማየት ነው። ተቻችሎ ፣ተዋድዶ፣ታግሎ ያታገለ፣እህት
ድርጅት፣ ምናምን የሚሉ ቃላቶች አፈር ድሜ ሲበሉ ማየት
ለደጋፊ ሀፍረት፤ ለተቃዋሚ ደስታ፤ለገለልተኛ ሰው ደግሞ ግራ
ነው።እዚህ ጋር ያቺ "ትበተናለች የተባለች ሃገር" የምትለው
ዲስኩት ጥያቄ ታስነሳለች። እንዳትበተን ያደረጋት ሀገራዊ አላማ
ይዞ የተነሳው ነው ወይስ የብሄር ጥያቄ የነበረው? ብለን
እንጠይቃለን።ይሄም የታሪክ ሽሚያ።በአንድ ድርጅት ውስጥ የእኔ
ነው ጥያቄ ሲነሳ እንዲህ ያሉ ጥያቄዎችም ይከተላሉ።ከጥያቄ
ስንወጣ፦ ሌላው "ሰው" የመሆን ምስጢር ከዘር እና ከአድሎ
የፀዳ መሆን ነው። ከዚህ መውጣት ያልቻሉት ሰው መሆን ደረጃ
ያልደረሱቱ በዘር ተተብትበው ጭንቅላታቸው ታውሮ የሚናገሩትን
እና የሚፅፉትን አያውቁም። ጉዋዶቻቸውን አጥተው ይህንን
ድርጅት እዚህ ያደረሱ ሰዎች ይህንን መሳይ ደጋፊ
ማፍራታቸውን ሲታዘቡ ምን እንደሚሰማቸው መገመት
አያዳግትም።ይህ የሚሆነው ግን እነሱ ከዚህ ስሜት( ከአጥንት
ቆጠራው) ከወጡ ብቻ ነው። ያለበለዚያ የቡድን ፅንፉ እየከረረ
ይቀጥልና ያልተተጠበቀ ውጤት ያመጣል። ለማንኛውም ግን
የአጥንት ቆጠራ ቡድናዊቱ ከሁለቱ ደጋፊዎች እንዳይጋባብን
እሰጋለሁ። የልዩነታችሁን ውበት ቁልጭ አድርጋችሁ
አሳይታችሁናልና እናመሰግናለን። "መሀል ሰፋሪ በአንድ ጥይት
ይመታል" እንደማትሉን ተስፋ አለን።መልካም ጌዜ።
ዛሬ ለሁላችሁም መሳደብም ጭምር ፈቅጃለሁ።

1 comment:

  1. I am actually thankful to the owner of this website who has shared this great post at here.
    umpan tikus

    ReplyDelete

Translate

About Me