Search This Blog

Sunday 30 July 2017

ቆጣስር

(የእሷ ባል የልጇ አባት ጠፍቶ ይህንን እያሰቡ ቢሆንስ)

ከአቡሸያ ጋራ ትመጣለህ ብለን
ጋራ ሸንተረሩን ሳንታክት አማትረን
ቅጠል በረገፈ ኮሽ ባለ ቁጥር
በብርሃን ፍጥነት ዞረን ስናማትር
አንተ ግን የለህም ድምፅህ አይሰማም
በኮሽታ ውስጥም መልዕክት አይደርሰንም።
እኔ ምን አውቃለሁ ልቤ እንዲህ ይለኛል
እንዳልተነካ ሰው ገላጋይ ይሆናል
በየተራራው ጥግ አስቤዛ ፍለጋ
ማጀቱን ለመሙላት ቀን ከሌት ስ'ተጋ (ስትተጋ)
ቀኝ አልቀና ብሎህ
ምን ይዤ ልመልስ ብለህስ እንደሆን?
እኔ ምን አውቃለሁ
ልጄም እንደ'ኔው ነው
በነጋ በጠባ ደጁን ያማትራል
እጆቹን አጣምሮ ሁሌም ይቆዝማል
የልጅነት ሆዱ ባብቶበት ይሆናል
አንዱ ልቤ ደግሞ
ከፋት ተሽከሞ
እንዲህ ይነግረኛል
የዚያ ሰፈር ሰዎች
የሆኑ ገብጋቦች
ሰብል ነክቶባቸው
ወጥመዱን ዘርግተው
ግድለውትስ ቢሆን?
አበስኩ ገበርኩ ሰይጣን አይስማብን
ጆሮውም ይደፈን
ና አማትብ አቡሽየ እንዳይሰማ ሰይጣን
ያደርገው ፈጣሪ ከእሱ በፊት ሞቴን
......
ሰይጣን የገባበት ግራ ጎኔ ደግሞ እንደዚህ ይለኛል
በወረደው ፀጉሩ በተንዘናፈለው
በሳንቃው ደረቱ እቀፉኝ በሚለው
ጎምለል ጎምለል ሲል ገብቶ ከቆንጆ አይን
ከሞላው ማጀቷቆጣስር ለማደር ገብቶላት እንዳይሆን?
(ለአዲስ አበቦዎች መፍቻ ቆጣ ስር= ወንድ በሴቷ ንብረት ለመተዳደር ቤቷ ሲገባ ቆጣ ስርነት ይባላል።)

No comments:

Post a Comment

Translate

About Me