Search This Blog

Sunday 30 July 2017

ኢትዮጵያ እንደ ቻይና


የባህረ ሰላጤው ሃገራት ኳታርን አየር ላይ ሲያንሳፍፏት፥ ኳታር ግራ ቀኙን ስታይ በዚያ ሳውዲ፣ በዚህ ግብፅ ፤ እና ደግሞ ዩናይትድ አረብ ኢሚሬቶች እና ባህሬን ሲያድሙባት አይኗን አሻግራ ጦቢያችን ላይ አሳረፈች። አሳርፋም አልቀረች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን "እንደ አሞራ በርርህ ጦቢያ ደርሰህ ና" አለችው። ሰውየው አዲስ አበበ ከተፍ አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያምን "ሃይለየ የባህረ ሰላጤው ሃገራት አደሙብን። ጁቡቲ እንኳ ከአቅሟ ከአነ ሳውዲ ጋር ሄዳ ተለጠፈች። አገራችሁ ከጎኔ ትሰለፍ ዘንድ እባክዎ ቃልዎትን ይስጡኝ" ብለው ለመኑ። ጦቢያየ በሃይልሻ በኩል "እኔ ሁላችሁችም ወዳጆቼ ናችሁ። ስለዚህ ችግራችሁን በዲፕሎሞሲያዊ መንገድ እንዲፈታ የተቻለኝን አደርጋለሁ" አለች። እደጊልኝ ጦቢያየ!! በቻይና እቀና የነበረው ዓለም ላይ ችግር ሲፈጠር እና ኃያል ነኝ ባዩዋ አሜሪካ " ቻይንየ ከጎኔ ተሰለፊ" ስትላት "ጉዳዩ በሰለም እንዲፈታ የበኩሌን አደርጋለሁ" በማለት የምትመልሰው ነገሯ ነበር። ባለፈው እንኳ ያ ትራምፕ የሚሉት ሰውየ በሰሜን ኮሪያ ላይ ደነፋ ደነፋ እና ምንም ማደርግ ሲያቅተው "ቻይና ምነው ዝም አልሽ?" ሲላት ቻይንየ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል "የሰሜን ኮሪያ የኒውክለር ጉዳይ አሳስቦኛል። በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈታም የበኩሌን እወጣለሁ" አለች። ማን በሰው ጉዳይ ፈትፍቶ ቂም ይሸምታል? የሰሞኑ በኳታር የኢትዮጵያ አቋምም ልክ እንደ ቻይንየ ተመችቶኛል። "ጉዳዩ በሰላም እንዲፈታ ኢትዮጵያ የበኩሏን ትወጣለች።" አለቀ!!
እንዲየው ከጭቆና አትቁጠሩብኝ እንጂ እኔ ግን ስለ ኳታር ትንፍሽ ሳይል በሌሎች ሃገራት የውስጥ ጉዳይ ገብቶ እየፈተፈተ ያስቸገረው አልጄዚራ ላይ ሁሉም ሃገራት ተባብረው አፉን ቢያዝጉት እንዴት ደስ ባለኝ። BBC እኮ በውጭ ሃገራት ላይ እንደፈለገ ቢዘል እንግሊዝንም ሳይምር ነው።

No comments:

Post a Comment

Translate

About Me